Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

sustainable

Sustainable DC
Governance
Equity
Built Environment
Climate
Economy
Education
Energy
Food
Health
Nature
Transportation
Waste
Water

Go Green - አማርኛ

Go Green  |   Español(Spanish)   |  Français(French)   |   አማርኛ(Amharic)   |   中国人(Chinese)   |   한국어(Korean)   |   Tiếng Việt(Vietnamese)

በዳሰሳ ጥናቶች እኛ የማህበረሰብ ማድመጫ ክፍለ-ጊዜያት አማካኝነት፣ የዲስትሪክቱ ኗሪዎች ዲስትሪክቱን የበለጠ ጤናማ፣ አረንጓዴ፣ እና ለመኖር ምቹ ቦታ ለማድረግ ስለ “ጎ ግሪን"” የበለጠ ማወቅ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ከታች ያሉት “ጎ ግሪን" እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ እርስዎን ለመርዳት የተዘጋጁ መተግበሪያዎች እና ቁሳቁሶች ናቸው፣ ወደ ተግባር ለመግባት ምን ያህል ጥረት፣ የገንዘብ ቁሳቁሶች፣ እና መሰረተ-ልማት እንደሚያስፈልግ ላይ ተመስርተው እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
በዚህ ወር ሊተገብሩዋቸው የሚችሉ ዋና ዋና የሆኑ አምስት ድርጊቶች ምንድን ናቸው?

የመዝናኛ ቦታዎች አጠቃቀምን ማዳበር

  • የአካባቢ ትሬይለሮችን፣ ፓርኮች፣ እና የውሃላይ መዝናኛዎችንይጎብኙ።
  • በማህበረሰብዎ የመዝናኛ ማእከል የጤና እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ይሳተፉ።
  • በማህበረሰብዎ ውስጥ የእግር ጉዞ ወይም የብስክሌት መንዳት ክበቦች ውስጥ ይሳተፉ።
ሃብቶች እና /አገናኝ ሊንክ መግለጫ
Department of Parks and Recreation Programs የዲሲ ፓርኮችና መዝናኛ ማዕከላት ዲፓርትመንት ፣ ዓመት-ሙሉ የሚቆይ ፕሮግራሞች እና እንቅስቃሴዎችን በሁሉም እድሜ ክልል ላይ ላሉ ሰዎች በነጻ ያቀርባል። ለዳንስ ይስልጠና ክፍለ-ጊዜያት፣ የትምህርት-በኋላ ፕሮግራሞች፣ የአትክልት ቦታ ማስዋብ ክፍለ-ጊዜያት፣ እና ለሌሎች መመዝገብ ይችላሉ።
Find a Facility የመጫወቻ ሜዳ ለመፈለግ፣ ወይም የመዝናኛ ማእከልን የፓርኮች እና መዝናኛ መምሪያ ካርታዎችን ይጠቀሙ። ሁሉም አገልግሎቶች ለዲስትሪክት ኗሪዎች በነጻ ይቀርባል።
Find a Park በዲስትሪክት ውስጥ የእስቴትና ብሔራዊ ፓርኮችን ለማግኘት የፓርኮች እና መዝናኛ መምሪያ ካርታዎችን ይጠቀሙ።

ሰስተኔብል ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥ ሃብቶች:  Sustainable DC Topic(s):

ሃይልን ይቆጥቡ

  • መብራቶችን በማጥፋት፣ ጥቅም ላይ የሌሉ መሳሪያዎችን በመንቀል፣ ተከፍተው ላሉ መሳሪያዎች ብቻ ኤሌክትሪክ የሚያቀርቡ የሃይል ገመዶችን በመጠቀም፣የቤትዎን ቴርሞስታት የሙቀት መጠን በክረምት ጊዜ ዝቅ በማድረግ እና በበጋ ጊዜ ከፍ በማድረግ የሚፈልጉትን ያህል ብቻ ሃይል ይጠቀሙ።
  • እንደ መስኮቶችን ማሸግ እና በሮችን ሙቀት እንዳያወጣ መሸፈን የሚመሳሰሉ የሃይል-ቁጠባ እርምጃዎችን መተግበር።
  • የኤሌክትሪክት ክፍያዎችን በመገምገም እና የሃይል ኦዲት በማግኘት ለቤትዎ ሃይል ለመቀነስያሉ መልካም እድሎችን ይለዩ።
  • ሃይል ቆጣቢ (ብሉ ኤነርጂ ስታር) የስም ምልክት በመምረጥ የሃይል-ቁጠባ መተግበሪያዎችን እና ሌሎች ምርቶችን ይጠቀሙ።
  • እንደ ሶላር (የጸሀይ) እና የንፋስ ሃይል የመሳሰሉትን ንጹህ የሃይል ምንጮች ይጠቀሙ። .
ሃብቶች እና /አገናኝ ሊንክ መግለጫ
DC Power Connect ዩቲሊቲ/ፍጆታ ክፍያን የሚከፍሉ ከሆነ፣ እርሶጋ የሚመጣውየሃይል አቅርቦ ከየት አንደሚመጣ መምረጥ ይችላሉ።! በ ዲስትሪክት ኮሎምቢያፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሽን አማካኝነት የሚቀርበው የየዲሲ ፓወር ኮኔክት ድረገጽ የዲስትሪክቱ ኗሪዎች የሃይል መስጫ አማራጮችን እንዲያነጻጽሩ እና እንዲመርጡ ይረዳል።
DC Sustainable Energy Utility ሃይል ቆጣቢ ዕቃዎችን የ ዲሲ ሰስቴኔብል ኢነርጂ ዩቲሊቲ በመቆጠብ እና ሃይል ቆጣቢ ዕቃዎችን ለሚጠቀሙ የዲሲ ነዋሪዎች ገንዘብ ተመላሽ በማድረግና ሃይል ቆጣቢ መሳሪያዎን በማቅረብ ያግዛል
ENERGY STAR Products

 

ሃይል ቆጣቢ ዕቃዎችን ለማግኘትለበለጠ መረጃየዩ ኤስ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ ድረገጽን ይጎብኙ ፣
Solar for All የጸሀይ ሃይል (ሶላር) ለሁሉም (Solar for All) ዝቅተኛ- እስከ መካከለኛ-ገቢ ያላቸው የዲስትሪክት ቤተሰቦች ንጹህ ሃይል እንዲጠቀሙ የሚረዳ ፕሮግራም ነው፣ ላጤ የሆኑ ቤተሰብ ቤቶች ላይ የሶላር ፓኔሎችን በመትከል እና ብዙ የቤተሰብ አባል ላላቸው ህንጻዎች ውስጥ የሚኖሩ አካራዮችን እና ኗሪዎችን የሚፈይዱ የማህበረሰብ የሶላር ፕሮጀክቶች አማካኝነት።
Weatherization Assistance Program

 

የሃይል እና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ዌዘራይዜሽን እርዳታ ፕሮግራም (Weatherization Assistance Program) ቤታቸው የበለጠ ውጤታማ የሃይል አጠቃቀም እንዲኖረው በማድረግ ብቁ ለሆኑ ኗሪዎች የሃይል ክፍያዎችን ለመቀነስ ይረዳል።

ቀጣይነት ያለው ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥  

ውሃን መቆጠብ

  • በማይጠቀሙበት ጊዜ ውሃውንበመግዛት፣ የገላ መታጠቢያ ወቅት ጊዜን በማፋጠን ፣ ልብሶችን እና የኩሽና እቃዎችን በሙሉ ክምችቶች በማጠብ የሚፈልጉትን ያህል ብቻ ውሃ ይጠቀሙ።
  • እንደ ዝቅተኛ ፈሳሽ የገላ መታጠቢያ ውሃ ማውረጃዎች፣ የቧምቧ መክፈቻዎች፣ እና ሽንት ቤቶች ዓይነት ውሃን-የሚቆጥቡ ምርቶችን ይጠቀሙ።
  • በዝናብ ወቅት ማየዝናብ በርሜሎችን መጠቀም ፣ሀገር በቀል ዛፎችን በቤትዎ አካባቢ በመትከል የ ጎርፍ ውሃ ይከላከሉ።
ሃብቶች እና /አገናኝ ሊንክ መግለጫ
RiverSmart Homes የ ሪቨር ስማርት ፕሮግራም ከየጎርፍ ውሃ (ወደ መሬት ውስጥ መግባት ያልቻለ የዝናብ ውሃ) የተነሳ ከንብረቶቻቸውን ከብክለት ለመከላከል ፍላጎት ላላቸው የቤት ባለቤቶች የማበረታቻ ድጋፍን ያቀርባል።
WaterSense Products የዩ ኤስ. የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ ድረገጽን ይጎብኙ፣ ሰማያዊውን እና አረንጓዴውን የወተርሴንስ ሌብል መለጠፊያ ምልክት ካላቸው ውሃን እንዲቆጥቡ የሚረዱዎ ምርቶችን ለማግኘት።

ሰስቴኔብል ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥  

አስፈላጊ የሆኑትን ሃብቶች በሙሉ ይጠቀሙ

  • ጥቅም ላይ የዋሉ ቁሳቁሶችን መልሰው-ይጠቀሙ ወይም ለሚፈልጉ አካላት ይስጡ፣የኢሜይል ዝርዝሮች፣ ወይም ድረገጾች አማካኝነት በማግኘት አሳልፈው በመስጠት እና መልሰው-ዓላማ ላይ ያውሉ።
  • የዲስትሪክቱ ሃብትን የመልሶ-መጠቀሚያ መመሪያን ይወቁ ፣እና የሚችሉትን ነገር ሁሉ ቀለም እና ኤሌክትሮኒክስን ጨምሮመልሰው-ጥቅም-ላይ ያውሉ፣ ።
  • አደጋ ሊያስከትሉ የሚችል ቆሻሻ በማስወገድ ሃላፊነትዎን ይወጡ፣ እንደ ልዩ የመሰብሰቢያ ዝግጅቶች ወይም የከተማ ቆሻሻ ማስተላለፊያ ጣቢያዎች ዓይነትን።
  • የምግብ ተረፈ ምርቶችን ወደ ቆሻሻ ገንዳ መጣያ ከሚወረውሩ ወደሚችሉ ማጠራቀሚዎች ያከማቹ፣ እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል ሰለሚቻል።
መገልገያ እና ማስፈንጠሪያ/አገናኝ መስመር መግለጫ
Reuse DC ሪዩዝ ዲሲ የዲስትሪክቱ የቤት ቁሳቁሶች የት እንደሚጠግኑ፣ እንደሚለግሱ እና ሁለተኛ፡እጅ የቤት እቃዎችን መግዛት የሚችሉበት ማዕከል ነዉ።
eCYCLE DC ኗሪዎች በኤሌክትሮኒክስ ውስጥ ያሉ ውድ ዋጋ ያላቸው ሀብቶችን በመሰብሰቢያ ዝግጅቶች እና የመጣያ ጣቢያዎች አማካኝነት መልሰው-ጥቅም ላይ ማዋል ይችላሉ።
Fix-It Clinics የሃይል እና አካባቢ መምሪያ ኗሪዎች እቃዎችን መጠገን እና መልስ-መጠቀም ላይ መመሪያ ማግኘት የሚችሉባቸው ዝግጅቶችን ያቀናጃል።
Paint Stewardship Program ኗሪዎች ከስራ የተረፈ ቀለምን ለመልሶ-መጠቀም እና ተገቢ ስራዎች በዲስትሪክቱ ውስጥ በልዩ የቀለም መደብሮች የመጣያ ጣቢያዎች መጣል ይችላሉ።
Zero Waste DC የህዝብ ሥራዎች ዜሮ ቆሻሻ DC (Zero Waste DC) ተናሳሽነት የገበሬዎች ገበያ የምግብ ትርፍራፊዎችን ለመዳበሪያ የሚቀበሉበት፣ ኗሪዎች ጥቅም ላይ የዋሉ ቁሳቁሶችን መግዛት ወይም መለገስ የሚችሉባቸው ድርጅቶች፣ በተለምዶ ጥቅም ላይ የዋሉ ቁሳቁሶች እንዴት መልሶ-እንደሚጠቀሙ ወይም እንደሚያስወግዱ ላይ መፈለግ የሚችል መመሪያ፣ እና ሌሎች ላይ መገልገያዎችን እና መረጃን ለኗሪዎች ያቀርባል።

ቀጣይነት ያለው ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥  Food Waste

ተፈጥሮን መጠበቅ

  • ከዚህ በኋላ ጥቅም ላይ የማይውሉ ቁሳቁሶችን በተገቢው የቆሻሻ ወይም መልሶ-ለጥቅም ማዋያ እቃ ውስጥ ያስቀምጡ እና ቆሻሻን ሲያዩ ያንሱት።
  • ተፈጥሯዊ፣ ጉዳት-የሌላቸው መዳበሪያዎችን እና የተባይ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ለቤትዎ የግቢ መስክ ወይም የአትክልት ጓሮ ያንከባክቡ።
  • መዳቀያዎችን የሚጠቅም የተለያዩ ዛፎችን እና ነባር ተክሎችን ይተክሉ እና ነባር ዘሮችን፣ ተክሎችን፣ መሳሪያዎችን፣ እና መረጃን በመጋራት ጎረቤቶችዎ ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ ይርዱ።
  • የወንዝ መጽዳቶች እና መልሶ መስሪያ ፕሮጀክቶች ውስጥ ይሳተፉ።
ሃብቶች እና /አገናኝ ሊንክ መግለጫ
Adopt Your District “ብሎክን ማጽዳት”፣ “ፓርክ ማጽዳት”፣ ወይም “የወንዝ ማጽዳት ፕሮግራሞች አማካኝነት” (Adopt a Block, Adopt a Park, Adopt a Stream)፣ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ንጹህ እና የሚያስደስት አድርገው ማቆየት ላይ ቁርጠኛ መሆን ይችላሉ።
Native and Invasive Pollinator Plants የሃይል እና አካባቢ መምሪያ ነዋሪዎች ምን እንደሚያሳድጉ ለመወሰን እንዲችሉ ለመርዳት የነባር እና የሚወጋ የማዳቀያ ተክሎች ዝርዝር አለው።
Rooting DC Rooting DC ማለት የአካባቢ የከተማ አትክልተኞች መረጃ የሚጋሩበት እና ከእርስ በርሳቸው የሚማሩበት ነጻ የዓመታዊ ዝግጅት እና የኢንተርኔት ላይ ሀብት ነው።
Sustainable DC Volunteers ቀጣይነት ያለው DC በጎ ፈቃደኛ ፕሮግራም (Sustainable DC) የበጎ ፈቃደኝነት እድሎችን ለአካባቢ ድርጅቶች ያቀርባል፣ የማጽጃ እና የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክቶችን የሚያካትት።
Urban Garden Education Program የፓርኮች እና መዝናኛ መምሪያ ልዩ ተጨባጭ የከተማ አትክልት ማሳደጊያ ክህሎሮችን እና የአካባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረት የሚሰጡ ነጻ ስልጠናዎችን እና ትምህርቶችን ይሰጣል።.

ቀጣይነት ያለው ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥ 

የአካባቢ የቀጣይነት ፕሮግራሞች ውስጥ መሳተፍ

  • ቀጣይነት ያለው ዲሲ መጽሄቶች እንዲደርሱዎ ይመዝገቡ እና የዲስትሪክት ኗሪዎች ጎ ግሪን ውስጥ እንዲሳተፍይ የሚረዱ ፕሮግራሞችን ይከታተሉ።
  • በማህበረሰብዎ ውስጥ የቀጣይነት ዝግጅቶች እና ተግባሮች ላይ ይሳተፉ፣ የእራስዎን ምግብ እንዴት እንደሚያሳድጉ ላይ ስልጠና ማግኘት፣ ስለ አካባቢ የዱር እንስሳት ለመማር የጎረቤትነት ፌስቲቫል፣ ወይም የዲስትሪክቱ ወደ ፊት እጣ-ፈንታ ላይ ግብዓት የሚሰጥበት ዝግጅት ዓይነቶችን።
  • የአካባቢያዊ፣ እኩልነት፣ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን የሚያስተናግዱ ቀጣይነት ያለው ዲሲ ወይም ሌሎች ቡድኖች ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት ይሳተፉ እና ጓደኞችዎን ወይም ጎረቤቶችዎን ይዘው ይምጡ።
ሃብቶች እና /አገናኝ ሊንክ መግለጫ
Serve DC የከንቲባዋ የበጎ-ፈቃደኝነት እና አጋርነቶች ቢሮ Serve DC ይባላል፣ የአገልግሎት ቀናትን የሚያስተዳድር፣ ነዋሪዎችን ትርጉም ካለው የበጎ ፈቃደኝነት እድሎች ጋር የሚያገናኝ፣ እና አጋርነት እና ትብብርን የሚያቋቋም ነው።
Sustainable DC Newsletter ቀጣይነት ያለው ዲሲ መጽሔት በ ቀጣይነት ያለው ዲሲ 2.0 እቅድ፣ የዲስትሪክት ቀጣይነት ዜናዎች፣ የበጎ ፈቃደኝነት እድሎች፣ የሚመጡ ዝግጅቶች፣ እና የስራ እድሎች ላይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ የሚያቀርብ ወርሃዊ ኢሜይል ነው።
Sustainable DC Volunteers ቀጣይነት ያለው ዲሲ በጎ ፈቃደኛ ፕሮግራም የማህበረሰብ አባላት የ ቀጣይነት ያለው ዲሲ 2.0 እቅድ ግቦችን ለሚያሳኩ ድርጅቶች በበጎ ፈቃደኝነት በመሳተፍ ቀጣይነት ያለው ዲሲ ጋር እንዲሰሩ እድል ያቀርባል። የማህበረሰብ አባላት የበጎ ፈቃደኝነት እድሎችን የያዙ ኢሜይልን ለመቀበል መመዝገብ ይችላሉ።

ቀጣይነት ያለው ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥  

የአካባቢውን ኢኮኖሚ የሚደግፍ እና ምግብ ተወርውሮ እንዳይጣል የሚከለክል የምግብ ምርጫዎችን ያድርጉ

  • ምግቦችን አስቀድሞ ማቀድ፣ ይሸጥ እስከ" ቀናት ተብለው ከተዘረዘሩ በላይ ምግቦች ምን ያህል እንደሚቆዩ ማወቅ፣ እና ትርፍ ምግቦችን ሊጠቀሟቸው ለሚችሉ ድርጅቶች መለገስ ዓይነት አማራጮችን በመጠቀም ምግብን ወርውሮ መጣልን ያስወግዱ።
  • በዲስትሪክቱ ውስጥ ወይም አቅራቢያ ያደገ ምግብን ያግኙ (በ100 ማይል ክልል ውስጥ ቢሆን የተሻለ ነው)።
  • በጥገና ወይም በእጅ-ላይ መማር ላይ በማገዝ የማህበረሰብ ወይም ትምህርት ቤት አትክልት ስፍራን ይርዱ።
ሃብቶች እና /አገናኝ ሊንክ መግለጫ
DC Food Recovery Working Group የዲሲ ምግብ መመለሻ የሥራ ቡድን ምግብ እንዳይጣል እንዴት እንደሚደረግ ላይ መረጃ እና መገልገያዎች አሉት፣ የምግብ ልገሳዎችን የሚቀበሉ ጣቢያዎች ዝርዝርን ጨምሮ።
Department of Parks and Recreation Communal Farms የፓርኮች እና መዝናኛ መምሪያየሚተዳደሩ የማህበረሰብ እርሻዎች የማህበረሰብ አባላት ነጻ ምግብ የሚቀበሉባቸው፣ በጎ አድራጎት የሚያደርጉባቸው፣ እና የእጅ-ላይ ትምህርታዊ እድሎች ውስጥ የሚሳተፉባቸው መንገዶችን ያቀርብላቸዋል።
Map of DC Farmers Markets ይህ አገናኝ ካርታ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ፕሮግራም (Supplemental Nutrition Assistance Program, SNAP) እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች፣ በበጋ ወቅት አካባቢያዊና አዲስ ምርቶችን በቂ ተደራሽነት ለሌላቸው ነዋሪዎች የሚያቀርብ Produce Plus Direct ዓይነትን፣ የሚቀበሉ የአርሶ-አደሮች ገበያን ያሳያል።
Office of the State Superintendent of Education Shared Roots Program Shared Roots የዲስትሪክት ነዋሪዎችን በትምህርት ቤቶች፣ የማህበረሰብ የአትክልት ስፍራዎች፣ እና ጓሮዎች ውስጥ ከአዲስ ምግብ ማሳደጊያ/ማምረቻ እድሎች ጋር በማገናኘት ምግብ እንዲያሳድጉ ያበረታታቸዋል።

Tቀጣይነት ያለው ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥  

አካሄድዎን ይቀይሩ

  • በሚችሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ ተግባሮችዎ በእግር ይሂዱ ወይም ዊልቼይር፣ የበረዶ ላይ ማንሸራተቻ፣ ወይም ብስክሌት ተጠቀሙ።
  • መኪና መንዳት ብቸኛው አማራጭ በሚሆንበት ጊዜ፣ መኪና በሚያቆሙበት ጊዜ ሞተሩን ያጥፉ። አላስፈላጊ ቸልተኝነት የሰው ጤናን ይጎዳል፣ ብክለትን ይፈጥራል፣ እና ነዳጅ እና ገንዘብን ያበክላል።
  • ሲነዱ ወይም የመኪናዎን በር ሲከፍቱ በእግር ለሚሄዱ ወይም ለሚያሽከረክሩ ሰዎች ሰፊ ቦታን በመስጠት ደህንነት ያለው ጉዞን ያሳድጉ።
  • በተደጋጋሚ የሚሄዱበት መዳረሻ ለመሄድ የሜትሮሬይል እና የአውቶብስ መንገዶችን ይማሩ እና በእግር መሄድ ወይም ማሽከርከር ባማይቻልበት ጊዜ የህዝብ ትራንስፖርት ይጠቀሙ።
  • ወደ ሥራ ወይም ትምህርት ቤት ለመሄድ በጋራ ከሰዎች ጋር ይሂዱ(ካር ፑል ይጠቀሙ)።
ሃብቶች እና /አገናኝ ሊንክ መግለጫ
Engine Idling Information የሃይል እና አካባቢ መምሪያ ሲቆሙ የመኪና ሞተር ማጥፋት ያላቸው ጥቅሞችን በተመለከተ እና የንግድ ተሽከርካሪ የዲስትሪክቱን የጸረ-ቸልተኝነት ህግ ከጣሰ እንዴት ሪፖርት እንደሚደረግ ላይ መረጃን ለኗሪዎች ያቀርባል።
goDCgo goDCgo፣ የዲስትሪክቱ የትራንስፖርት መምሪያ ፕሮጀክት የሆነው፣ የትኞቹ የትራንስፖርት አማራጮች ቅነሳ እንደሚያደርጉ ላይ የአጠቃላይ እይታ ዓይነት ቁሳቁሶችን፣ በዲስትሪክቱ ውስጥ ብስክሌት መንዳት ላይ መረጃን፣ ሜትሮሬይል መንዳት እንዴት እንደሚጀመር ላይ መመሪያዎችን፣ እና የካርፖል (መኪና መሰብሰብ) ለማቀናጀት መሳሪያዎችን ያቀርባል።
Sidewalk Repair Requests የዲስትሪክት ነዋሪዎች ለከንቲባው ከተማ-ደረጃ የጥሪ ማእከል በ 311 እና (202) 727-1000 በመደወል፣ ወይም በኢንተርኔት የአገልግሎት ጥያቄን በመሙላት የመንገድ-ዳር ጥገና አገልግሎቶችን መጠየቅ ይችላሉ።

ቀጣይነት ያለው ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥  

የ ግሪን(አረንጓዴ) ተጠቃሚ ይሁኑ

  • ዝቅተኛ፣ ከላስቲክ-ነጻ እሽግ ያላቸው፣ ወይም ዳግም-ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ወይም ዳግም-ለጥቅም-መሰራት የሚችሉ እሽጎች ያላቸውን ቁሳቁሶች ይምረጡ።
  • ከሱቅ እቃ ሲገዙ የጨርቅ ቦርሳዎች፣ ዳግም-መሞላት የሚችሉ የውሃ ጠርሙሶች፣ መታጠብ የሚችሉ ስትሮዎች፣ እና ፍራፍሬዎች እና አትክልቶችን በፊሪጂ ውስጥ ለማስቀመጥ የሚሆኑ የወንፊት ቦርሳዎች ዓይነት ዳግም-ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ምርቶችን ይጠቀሙ።
  • የተፈጥሮ፣ ጉዳት-የሌላቸው የግል መንከባከቢያ ምርቶችን ይጠቀሙ።
  • Shop Local DC Directory (ከአካባቢው ይግዙ የዲሲ ዳይሬክተሪ) ውስጥ በተዘረዘሩ ዓይነት በአካባቢ የአረንጓዴ ንግድ ቤቶች ይሸምቱ።
ሃብቶች እና /አገናኝ ሊንክ መግለጫ
District of Columbia Sustainable Specifications የኮንትራት እና የግዢ ቢሮ አንዳንድ ምርቶች ቀጣይነት ይላቸው ግዢዎች ተብለው ለመወሰድ ማሟላት የሚገባቸው ልዩ መግለጫዎችን አዘጋጅቷል። ምንም እንኳ በዲስትሪክት ኤጀንሲዎች የሚፈጸሙ ግዢዎችን ለመምራት የተዘጋጁ ቢሆኑም፣ ኗሪዎችም ልዩ መግለጫዎቹን መገምገም እና ምርቶችን ሲገዙ ተመሳሳይ ባህሪያትን መፈለግ ይችላሉ።
Shop Local DC Directory የትናንሽ እና የአካባቢ የንግድ እድገት መምሪያ የShop Local DC Directoryን ያስተዳድራል፣ የአካባቢ የአረንጓዴ ንግዶችን የመፈለግ አማራጭን ጨምሮ።
Zero Waste DC የዲሲ ፑብሊክ ዎርክስ ደፓርትመንት የዜሮ ዌስት ዲሲ (Zero Waste DC)ተነሳሽነት ግዢ ሲፈጽሙ ቆሻሻን እንዴት እንደሚቀንሱ ላይ፣ ከዚህ በፊት በምርቶች የተያዙ የነበሩ የሱቆች ዳይሬክተሪን ጨምሮ፣ መረጃን ለኗሪዎች ያቀርባል።

ቀጣይነት ያለው ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥  

ለከባድ የአየር ሁኔታ ይዘጋጁ

  • በከባድ የአየር ሁኔታ ጊዜ ቤተሰብዎን በደህንነት ለማቆየት የድንገተኛ ጊዜ ኪትን ያዘጋጁ።
  • የዝግጁነት እቅድን ያዘጋጁ እና መተግበሩን ይለማመዱ፣ በከባድ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ወቅት ቤተሰብዎ ምን ማድረግ እንዳለበት እንዲያውቅ።/li>
  • የቤትዎ ወይም የአካራይዎ መድን በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት የደረሰ ጉዳትን እንዴት እንደሚያስተናግድ ይፈትሹ እና ጥያቄ ለማቅረብ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ይሰብስቡ፣ እንደ ይዞታዎችዎን መቁጠር ዓይነት።
ሃብቶች እና /አገናኝ ሊንክ መግለጫ
ReadyDC Emergency Kit እርስዎን እና በቤተሰብዎ ውስጥ ያሉ ሌሎች ሰዎችን ብደህንነት ለማቆየት በድንገተኛ ጊዜ ኪት ውስጥ ማካተት ስላለብዎ ቁሳቁሶች ይማሩ፣ በሀገር ደህንነት እና ድንገተኛ ሁኔታ አስተዳደር ኤጀንሲ የቀረበውን ይህንን ዝርዝር በመጠቀም።
ReadyDC Family Emergency Plan በሀገር ደህንነት እና ድንገተኛ ሁኔታ አስተዳደር ኤጀንሲ የቀረበውን መመሪያ በመጠቀም ከጊዜ አስቀድመው ለድንገተኛ ሁኔታዎች እንዴት እንደሚዘጋጁ ይማሩ። አካል ጉዳተኛ እና አረጋውያን ለሆኑ ሰዎች ልዩ መመሪያዎች አሉ።

ቀጣይነት ያለው ዲሲ ርዕስ(ሶች)፥